ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የሕፃናትና የታዳጊ ወጣቶች ትምህርት ክፍል

የወላጅ ኃላፊነትና ግዴታ ስምምነት ሰነድ
2026–2027

1. መንፈሳዊ መሠረት፦ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” በሚለው መለኮታዊ ቃል መሠረት ልጆች ፈርሃ እግዚአብሔር አድሮባቸው እንዲያድጉ በትጋት እጥራለሁ።
2. የሰዓት አክብሮትና ቁሳቁስ፦ ልጄን በየሳምንቱ ሳያቋርጥ የሚያስፈልገውን የትምህርት ቁሳቁስ አሟልቼ በሰዓቱ አምጣለሁ፤ ትምህርት ሲያልቅም በተወሰነው ሰዓት እወስዳለሁ።
3. የቤት ሥራ ክትትል፦ በየሳምንቱ የሚሰጠውን የቤት ሥራ በጥንቃቄ በመከታተልና በመርዳት አሰራለሁ። ይህንንም ማድረጌን በቤት ሥራው ወረቀት ላይ በፊርማዬ አረጋግጣለሁ።
4. የቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አለባበስ፦ ቤተ ክርስቲያን የተከበረና የተቀደሰ ቦታ መሆኗን በመገንዘብ ልጄ ለቤተ ክርስቲያን የሚገባና የተገቢነት ሥርዓት ያለውን ልብስ ለብሶ ትምህርት እንዲከታተል አደርጋለሁ።
5. በክፍል ውስጥ ተሳትፎ፦ ከልጄ አስተማሪዎች ጋር በመመካከር በልጁ ክፍል ውስጥ በተራዬ በመገኘት (በመቀያየር) የሚያስፈልገውን ማንኛውንም እርዳታ እሰጣለሁ።
6. በስብሰባዎች መገኘት፦ በአስተማሪዎችም ሆነ በትምህርት ክፍሉ የወላጅ ኮሚቴ የሚጠራውን ስብሰባ ሁሉ በሰዓቱ ተገኝቼ እካፈላለሁ።
7. የኮሚቴ ተሳትፎ፦ የወላጅ ኮሚቴ በሚያስተባብራቸው በተለያዩ የትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴዎች ውስጥ በመመዝገብ ለልጄ ትምህርት ስኬት የበኩሌን አስተዋፅኦ አደርጋለሁ።
8. የአካዳሚክ መመዘኛ እና የቦታ ጥበት፦ ልጄ ከትምህርት ክትትል በኋላ የሚሰጠውን መመዘኛ (ፈተና) ማለፍ ካልቻለ፣ በቦታ ጥበት ምክንያት በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እንደገና የመድገም ዕድል እንደማያገኝና ቦታው ለሌላ ልጅ እንደሚሰጥ እገነዘባለሁ።
9. የመቅረት ደንብ፦ ልጄ በአንድ ሴሚስተር ውስጥ ከ 4 ጊዜ በላይ በክፍል ካልተገኘ (2 ቀን በፈቃድ እና 2 ቀን ያለፈቃድ) የትምህርት ክፍሉ ቦታውን በተጠባባቂነት (Waiting List) ላይ ላሉ ወላጆች አሳልፎ እንደሚሰጥና ተማሪውም ቦታውን እንደሚያጣ እስማማለሁ።
10. የዲሲፕሊን ሥርዓት፦ ልጄ የዲሲፕሊን ችግር እንዳለበት በመምህሩና በትምህርት ክፍሉ ከተረጋገጠ፣ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ጉዳዩን መርምሮ ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል። እርምጃው እንደ ጥፋቱ መጠን እስከ ትምህርት ማባረር ሊደርስ እንደሚችል እገነዘባለሁ።
11. ቅሬታ አፈታት፦ በልጄ እና በመምህሩ /ሯ መካከል ማንኛውም ዓይነት ችግር ከተፈጠረ ጉዳዩን ለትምህርት ክፍሉ በወቅቱ አሳውቃለሁ። መምህሩን /ሯን በተናጠል በቀጥታ ለማናገር ፍጹም ሙከራ አላደርግም።
12. የመጽሐፍ አያያዝ፦ ለልጄ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ የተሰጠውን የመማሪያ መጽሐፍ በጥንቃቄ እይዛለሁ። መጽሐፉ ቢቀደድ ወይም ቢጠፋ የተሰላውን ሙሉ ዋጋ በመክፈል ሌላ ቅጂ (Copy) እንዲሰጠኝ እጠይቃለሁ።

ከላይ የጻፍኩት የወላጅ/አሳዳጊ ስም የእኔ መሆኑን እና ሙሉ ስሜን ከዚህ በታች በመጻፍ ይህንን ስምምነት በኤሌክትሮኒክ ፊርማዬ እንደተቀበልኩ አረጋግጣለሁ። By typing my full name below, I confirm that I am the Parent/Guardian identified above and that my typed name represents my electronic acknowledgment and acceptance of this agreement.